ለኣሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት በሙሉ



በቅድሚያ የማክበር ስላምታችንን እያቀረብን February 1, 2025 በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ውሳኔ ተከትሎ፣ ጥገኛ ወላጆችን  ወደ  ሙሉ አባል  ለማሸጋገር  ለእድሩ አባላት በሙሉ June 1, 2025 ማስታወቂያ ተልኳል። ይህን ምዝገባ ለማጠናቀቅ የጊዜ ገደብ እስከ June 30, 2025 ተሰጥቶ  ነበር:: (የመጀመርያው መልእክት ለማጣቀሻ ከዚህ በታች ተያይዟል።) ነገር  ግን እስከ አሁን ድረስ ይህን የምዝገባ ሂደት ያጠናቀቁት ጥቂት አባላት ብቻ ናቸው። ስለዚህም የእድሩ ኮሚቴ የምዝገባ  ቀነ  ገደቡን ለማራዘም ተገዷል:: በዚህም  መስረት ይህን ሁለተኛ ማስታወቂያ እያስተላለፈ ነው። የምዝገባ   ቀነ  ገደቡ  እስከ  September 30, 2025 ድረስ  ተራዝሟል:: አባላት በሙሉ እስከ September 30, 2025 ድረስ የጥገኛ ወላጆቻቸውን ምዝገባ ካላጠናቀቁ ወላጆች የአባልነት ጥቅሞችን እንደሚያጡና  ከአባልነታቸው  በፈቃዳቸው  እንደተሰናበቱ  በማክበር  እናሳስባለን። ከዚህ የመጨረሻ ማራዘሚያ ጊዜ በኋላ, ጥገኛ ወላጆች  እድሩን ለመቀላቀል ከመረጡ እንደ  አዲስ  አባል የመመዝገቢያ  ክፍያ  ከፍለው እና  የይርጋ  ጊዜ ጠብቀው መመዝገብ   ይችላሉ::

የአባልነት ቅጾች በባቲ ባዛር  የናት እንጀራ በአባተ ድራር ኢንሹራንስ እና ኬር ሬስቶራንት ይገኛሉ. እባክዎ ቅጾቹን ሞልተው በእነዚህ ቦታዎች ወይም ከታች ለተዘረዘሩት የእድር ኮሚቴ አባላት ለአንዱ ስጧቸው።

የአባልነት  ቅጽ  በ Arizona Meredaja Andnet Edir telegram ገጻችን  ላይ  ይገኛል:: ስብስክራይብ  ለማድረግ  ይህንን  ሊንክ  ይጠቀሙ https://t.me/+bprgm34mzvMwZGEx

ስለትብብሮ እናመሰግናለን

የእድሩ  ኮሚቴ




Greetings to all members of the Edir,

As you might remember, communication was sent on June 1, 2025 to register your dependents per the decision made at the General Assembly meeting held on Feb 1, 2025. The deadline to complete the registration was June 30, 2025. (The original communication is attached below for reference). To date, few members have completed this registration process. The AZEdir committee is sending this second notice to extend the deadline to complete the registration until September 30, 2025. Please be advised that if a member has not submitted the membership application for his/her dependent registration by September 30, 2025, the dependent will forfeit all membership benefits. After this final extension period, if the dependent decides to join the Edir, all requirements of a new member will apply. The dependent will have to pay the registration fee and will be subjected to the 90-days waiting period. Please submit your dependent application to one of the AZEdir committee members or drop your completed application at one of these locations.

Membership forms are available at Bati Bazar, Yenat Injera, ADRAR Insurance and KARE Restaurant. Membership application is also available at our Arizona Andnet Meredaja Edir telegram page. Please subscribe to this page if you have not done so already at this link – Telegram: Join Group Chat

We appreciate your cooperation!

AZEdir Committe



June 1, 2025. የተላከው  የምጀመሪያው  መልእክት

First communication sent on June 1, 2025

ለአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት በሙሉ:

በቅድሚያ የማክበር ስላምታችንን እያቀረብን ከዚህ በፊት ወላጆች በልጆቻቸው ስር ሆነው የእድር አገልግሎት ያገኙ እንደነበር ይታወቃል ሆኖም ግን በ Feb 1/2025 ባደረግነው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ወላጆች የእድሩ እንደ ግለሰብ አባል እንዲቆጠሩና የሞት አደጋ በሚደርስበት ጊዜ የሚገባውን ክፍያ እንዲከፍሉ እንዲሁም እንደ ሌላው አባል ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ተወስኗል::በዚህም መሰረት የጥገኛ አባላትን (ወላጆችን) ወደ ግለሰብ አባላት የማሸጋገር ሂደቱን ለመጀመር፣ ጥገኛ ወላጆቻቸው ያሏቸው አባላት ወላጆቻቸውን የአባልነት ቅጹን እስከ June 30, 2025 ድረስ በማስሞላት እንዲያጠናቅቁ በማክበር እንጠይቃለን።

የአባልነት ቅጾች በባቲ ባዛር, የናት እንጀራ በአባተ ድራር ኢንሹራንስ እና ኬር ሬስቶራንት ይገኛሉ. እባክዎ ቅጾቹን ሞልተው በእነዚህ ቦታዎች ወይም ከታች ለተዘረዘሩት የእድር ኮሚቴ አባላት ለአንዱ ስጧቸው።

የእድር ኮሚቴ አባላት ቅጾቹን ከሰበሰቡ እና ካረጋገጡ በኋላየወላጆን የአባልነት መታወቂያ ቁጥር ይሰጡዎታል::

ይሄንን ሂደት የማመልከቻ ክፍያ እና የይርጋ ጊዜ(90 days waiting period) አይመለከተውም

ጥያቄ ካሏት ከነዚህ እድር አባላት አንደኛቸው ጋር ቴክስት መልእክት ይላኩ

Tigist Bedane – 602-751-9548

Tesfaye Enaro – 602-516-0273

Denahun Desta – 602-373-1230

Tinsae Babo – 602-703-7497

Woldu Kidane – 602-510-5674

 

To all members of the Arizona Andenet Edir:

Greetings to all members of the Edir,

It is known that in the past, parents received the benefits of the Edir as dependents of members. However, at the general assembly meeting held on Feb 1/2025, it was decided that parents should be considered as individual members of the Edir and pay the due payment in the event of a death and receive full benefits like other members. Accordingly, in order to start the process of transitioning dependent members (parents) to individual members, we need current members to have their dependent parents complete the membership form by June 30, 2025. Membership forms are available at Bati Bazar, Yenat Injera, ADRAR Insurance and KARE Restaurant. Please complete the forms and leave at these places or give to one of the Edir Committee members listed below. Edir Committee members will collect the forms and after they review, they will contact you with your parent’s member ID. Please note that application fee and waiting period do not apply for this process.

If you have any questions, please text the following Edir committee members.

Tigist Bedane – 602-751-9548

Tesfaye Enaro – 602-516-0273

Denahun Desta – 602-373-1230

Tinsae Babo – 602-703-7497

Woldu Kidane – 602-510-5674

Arizona Andenet Edir Committee