05/12/2021   

1ኛ/ የመመዝገቢያ እና የአባልነት ክፍያ ለአንድ ሰው $ 300 ለባል እና ሚስት $ 600.00 ዶላር

ተብሎ የተወሰነው፤ ወደ ነበረበት አንድ ሰው $ 125.00 ባል እና ሚስት $ 250.00 እየከፈሉ

የእድሩ አባላት እንዲሆኑ፤

 2ኛ/ አባላት በስራቸው በጥገኝነት ያስመዘገቧቸው ልጆቻቸው 21 ዓመት ሲሞላቸው ከእድሩ እንደሚሰናበት ወይም መመዝገቢያ እና የአባልነት $ 125 ዶላር ከፍለው አባል ሊሆኑ ይችላሉ የሚለውን ውሳኔ በማሻሻል 21 ዓመት ሲሞላቸው ያለምንም ክፍያ በነጻ አባል ወይም አባላት መሆን እንደሚችሉ በእለቱ አመራሩ በሁኔታው አምኖ አሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት November 30/2020 ዓ/ም  በዙም በተደረገ የጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የመመዝገቢያ እና የአባል ክፍያ በነፍስ ወከፍ ሶስት መቶ ($ 300.00) ዶላር ባል እና ሚስት $ 600.00 ዶላር ክፍለው አባል መሆን እንደሚችሉ መወሰኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ አጠቃላይ ሁኔታውን ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ በመሆኑ የእድሩን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ አዳክሞታል። ከNovember 30/2020 ዓ/ም ጀምሮ በዚህ 6 ወር ውስጥ ከአንድ  አዲስ ተመዝጋቢ አባል በስተቀር አዲስ የተመዘገበ አባል የለም ለማለት ይቻላል። በተለያዩ ምክንያቶችም ከሚለቁ አባላት ጋር ተደምሮ የእድሩ እድገት አንድ ቦታ ላይ እንዲቆም አድርጎታል። ይህም ሁኔታ የእድሩን አመራር እጅግ ስላሳሰበው የእድሩ አመራር አባላት በ 04/23/21 ዓ/ም ተሰብስበው ችግሩን በሚገባ አብላልተው ተወያይተውበት፤ የእድሩን ሕልውና ለመታደግ ሲባል የሚከተሉትን ሁለት ውሳኔዎች ወስኖ ስራ ላይ የአዋለው መሆኑን በታላቅ አክብሮት ያሳውቃል። ውሳኔዎቹ

የተስማማ መሆኑን  በአክብሮት አያሳወቅን ይሁን አንጅ የመላ አባላት በዉሳኔው ተሳታፊ መሆን ስላለበት  መላ አባላትም ይህን ዉሳኔ ለአድራችን አንደምበጅ በማመን ትደግፉታላችሁ ብለን አናምናለን ይሁን አንጅ ይህን ዉሳኔ የማይደግፍ አባል ካለ በስልክ ወይም በደብዳቤ  አስከ  05/20/2021 አንድታሳዉቁን አና በድምጽ ብልጫ ዉሳኔዉን ተግባራዊ አንድናደርግ በትህትና አናሳስባለን:: 

ከሰላምታ ጋር

ተድላ አብርሃም

የአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር ሊቀመንበር