ለአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት በሙሉ
ጉዳዩ፡ በኮቪድ 19 ቀሳፊ በሽታ ምክንያት ለረዥም ጊዜ የተጓተተዉን አመታዊ ስብሰባ ለማድረግ መቻሉን እና መወሰን ይመለከታል።
በርእሱ እንደተገለጸው የአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አመታዊ ስብሰባ በአመት አንድ ጊዜ መደረግ እንዳለበት በእድሩ መተዳደሪያ አንቀጽ ቁጥር 15-2 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፤በየአመቱ በሚደረግ ስብሰባ አባላት ስለ እድሩ አሰራር እድገት ይመክራሉ ችግሮች ከተከሰቱ በወቅቱ ይፈታሉ።
እንዳለመታደል ሆኖ በአለፉት ዓመታት ዓለምን ያመሰዉ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የእድሩ አባላት ተሰብስበው ስለ እድሩ እድገት ሊመክሩ አልቻሉም፤ በተከሰቱ ችግሮችም ላይም መፍትሄ መስጠት አልቻሉም በዚህም ምክንያት የእድሩን ህልዉና የሚፈታተን ችግሮች ሊቀረፉ ወይም ሊፈቱ ባለመቻሉ ሲጓተቱ አመታት አስቆጥረዋል ፤ በዚህ ወቅት ችግሮች ከአልተፈቱ እንቅስቃሴዉንም በተሟላ መልኩ ማስቀጠል አይቻልም; የእድሩንም ህልዉና ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባው ይሆናል።ስለዚህ አባላት ከታች በተጠቀሰው ቀን ሰዓትና ቦታ በመገኘት አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።የጠቅላላ ጉባኤዉን ዉሳኔ የሚሹ (የሚጠብቁ) አጀንዳወች ስላሉ በእነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ጉባኤው የማያዳግም ዉሳኔ ለመስጠት እንዲያስችለው ይህንን ስብሰባ መጥራት አስፈልጓል።
የእለቱ አንገብጋቢ አጀንዳወች
1. የእድሩ አባል የነበሩ የአቶ ሹምየ ገ/ማርያም አሟሟት ሁኔታ እና የክፍያ ጥያቄን በተመለከተ ዉሳኔ መስጠት፤
2. በማገልገል ላይ የሚገኘው የአመራር ኮሚቴ የእድሩ ደንብ ከሚፈቅደው የአገልግሎት ዘመን በላይ እያገለገለ ያለ በመሆኑ የምርጫ ሂደት እንዲከናወን፤
3. አመራሩ አስመራጭ ኮሚቴ አቋቁሞአል አመራሩ ያቋቋመዉ አስመራጭ ኮሚቴ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶ ሁሉንም የእምነት ቢቶች የዳሰሰ ሁሉን አቀፍ የሆነ ስራ በመስራት ተረካቢ እጩ አመራሮችን ነቅሶ በማዉጣት ብጥራት ተረካቢ እጩ 9 (ዘነኝ) የአመራር አባላትን 3)ሶስት) እጩ የቁጥጥር እና ኦዲት ኮሚቴ አባላትን አዘጋጅቷል በመሆኑም ጉባኤው መርምሮ እንዲያጸድቅ ይጠይቃል።
4. በመተዳደሪያ ደንቡ ላይም በጥቂት አንቀጾች ላይ የተደረገዉን መሻሻል መርምሮ ማጽደቅ ሲሆኑ የእድሩ አባላት በ እለቱ ተገኝተው ለቀረቡት ጉዳዮች የማያዳግም መፍትሄ የመስጠት ሐላፊነት ያለባቸው በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቦታና ሰአት እንድትገኙ በአመራር ኮሚቴ ስም ይህን መልእክት በትልቅ ትህትና አስተላልፋለሁ።
ከሰላምታ ጋር አቶ ተድላ አብርሃም
የእድሩ አመራር ኮሚቴ ሰብሳቢ
ቦታ፡ Embassy suite Hotel
አድራሻ፡ 2333 E Thomas Rd phoenix Arizona 85016
ቀን ፡ March 26,2022
ሰዓት፡ 3:00 PM
