ለአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት በሙሉ:
በቅድሚያ የማክበር ስላምታችንን እያቀረብን ከዚህ በፊት ወላጆች በልጆቻቸው ስር ሆነው የእድር አገልግሎት ያገኙ እንደነበር ይታወቃል ሆኖም ግን በ Feb 1/2025 ባደረግነው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ወላጆች የእድሩ እንደ ግለሰብ አባል እንዲቆጠሩና የሞት አደጋ በሚደርስበት ጊዜ የሚገባውን ክፍያ እንዲከፍሉ እንዲሁም እንደ ሌላው አባል ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ተወስኗል::በዚህም መሰረት የጥገኛ አባላትን (ወላጆችን) ወደ ግለሰብ አባላት የማሸጋገር ሂደቱን ለመጀመር፣ ጥገኛ ወላጆቻቸው ያሏቸው አባላት ወላጆቻቸውን የአባልነት ቅጹን እስከ June 30, 2025 ድረስ በማስሞላት እንዲያጠናቅቁ በማክበር እንጠይቃለን።
የአባልነት ቅጾች በባቲ ባዛር, የናት እንጀራ በአባተ ድራር ኢንሹራንስ እና ኬር ሬስቶራንት ይገኛሉ. እባክዎ ቅጾቹን ሞልተው በእነዚህ ቦታዎች ወይም ከታች ለተዘረዘሩት የእድር ኮሚቴ አባላት ለአንዱ ስጧቸው።
የእድር ኮሚቴ አባላት ቅጾቹን ከሰበሰቡ እና ካረጋገጡ በኋላየወላጆን የአባልነት መታወቂያ ቁጥር ይሰጡዎታል::
ይሄንን ሂደት የማመልከቻ ክፍያ እና የይርጋ ጊዜ(90 days waiting period) አይመለከተውም
ጥያቄ ካሏት ከነዚህ እድር አባላት አንደኛቸው ጋር ቴክስት መልእክት ይላኩ
Tigist Bedane – 602-751-9548
Tesfaye Enaro – 602-516-0273
Denahun Desta – 602-373-1230
Tinsae Babo – 602-703-7497
Woldu Kidane – 602-510-5674