ለአሪዞና አንድነት መረዳጃ እድር አባላት በሙሉ፣
የእድራችን አባል የወ/ሮ ዘውዲቱ አለሙን ሕልፈተ ሕይዎት አስመልክቶ በ 2/26/2024 ከእድሩ $15,000 dollar ወጭ ተደርጏል፣ ይህን ወጭ ለመተካት፣ እያንዳንዱ አባል $35 dollar እንዲከፍል ተወስኗል:: ይህንን ክፍያ ከ 3/11/24 እስከ 4/10/24 $35 ከ 4/11/24 እስከ 4/26/24 ደግሞ እስከመቀጫው $60 እንዲከፍሉ በትህትና እናሳስባለን::
በዚህ ጊዜ ክፍያውን ያልከፈለ አባል ቢኖር፣በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10,2.3መሰረት፣ በራሱ ፈቃድ ከእድሩ የሚወጣ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን። የእድሩ ኮሚቴ ክፍያ መደራረቡን እና ለአባላት ከባድ ሊሆን እንደሚችል በማገናዘብ ጠቅላላ መዋጮውን ለማሳነስና የመክፈያ ጊዜውን ለማራዘም ሞክሯል:: ከዚሁ ጋር በዚህ እድር እማካኝነት እርስበርሳችን ለመረዳዳት እድል ስላገኘን ፈጣሪንእናመሰግናለን::
ክፍያ ለመክፈል፣
1. AZedir.org online (Click Make payment bellow)
2. በ Zelle ARIZONA ANDINET MEREDAJA በዚህስልክ ቁጥር ይክፈሉ፣ 6234990428 (እባክዎ ሙሉ ስምዎትንና የአባል ቁጥርዎትን (ለሌላ አባል ከከፈሉም የአባሉን ስምና የአባል ቁጥሩን) በሜሞ (memo) ሳጥኑ ውስጥ እንዲጽፉ በአክብሮት እንጠይቃለን
3. ዌልስ ፋርጎ ባንክ አካውንት #7330133609 ሪሲቱ ላይ ስምዎትን ጽፈው በ 6027542506 ቴክስት እንዲያደርጉ በትህትና እናሳስባለን፣
4. ባቲ እና የእናት እንጀራ ሱቆች መክፈል ይቻላል።