የእድራችን አባላት የሆኑት የወ/ሮ ሮማን ጄማን እና የአቶ አለማየሁ አለምነህን ሕልፈተ ሕይዎት አስመልክቶ በ3/7/25 እና በ3/9/25 ከእድሩ 30,000 ዶላር (ለእያንድ አንዳቸው 15,000 ዶላር) ወጭ ተደርጏል። ይህን ወጭ ለመተካት፣ እያንዳንዱ አባል $70 እንዲከፍል ተወስኗል:: በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10.1 እና አንቀጽ 10.2 መሰረት ከ 3/18/25 እስከ 4/18/25 $70.00 ያለመቀጫ፣ ከ4/19/25 እስከ 5/5/25 ደግሞ ከ$25.00 መቀጫ ጋር $95.00 እንዲከፍሉ በትህትና እናሳስባለን:: በዚህ ጊዜ ክፍያውን ያልከፈለ አባል ቢኖር በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 10.2 እና 10.3 መሰረት፣ ከእድሩ የወጡ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።
የክፍያ መንገዶች፦
በ Online ለመክፈል azedir.org ላይ Make Payment የሚለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
በ Zelle ለመክፈል የARIZONA ANDINET MEREDAJA EDIR ስልክ ቁጥር የሆነውን 623-499-0428 ይጠቀሙ። በZelle ክፍያ የሚፈጽሙ ከሆነ ሙሉ ስምዎትንና የአባል መለያ ቁጥርዎትን፤ ለሌላም አባል የሚከፈሉ ከሆነ የአባሉን ስምና የአባሉን መለያ ቁጥሩን በማስታወሻ ሳጥን (Memo Box) ውስጥ እንዲጽፉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በቀጥታ ባንክ ማስገባት ከፈለጉ የ ዌልስ ፋርጎ ባንክ አካውንታችንን Account Number 7330133609 እና Routing Number 122105278 ይጠቀሙ። የከፈሉበት ደረሰኝ ላይ ስምዎትን ጽፈው ፎቶ በማንሳት 623-499-0428 ላይ ቴክስት እንዲያደርጉ በትህትና እናሳስባለን።
በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ባቲ ባዛር እና የእናት እንጀራ ሱቆች መክፈል ይቻላል።
ስለአባልነትዎ እናመሰግናለን
የእድሩ ኮሚቴ
The Edir has disbursed $30,000 on 3/7/2025 and 3/9/25 to cover the funeral expenses of our members W/ro Roman Jemma and Ato Alemayehu Alemneh $15,000, respectively. As outlined in the Bylaws of the Edir, this expense shall be allocated to the remaining qualifying and active members. Accordingly, it was decided that each member’s contribution would be $70.00. We kindly request that each active member pay $70.00 from 3/18/2025 to 4/18/2025 without penalty and $95.00, including a penalty of $25.00 from 4/19/2025 to 5/5/2025, in accordance with Article 11 of the Bylaws.
Please note that, per Article 11 of the Edir’s bylaws, members who do not complete the required payment within the mentioned time frame will forfeit their membership status.
Here are the available payment methods:
We appreciate your membership!
AZ Andnet Meredaja Edir Committee